ሰዎችን ቅድሚያ የሚሰጥ መድረክ

ጃኒዝ ሉዊስ ጆርጅ ለዲሲ ከንቲባነት እየተወዳደረች ያለችው ዲሲ ከቤት ኪራይ እስከ ህፃናት እንክብካቤ ድረስ በጣም ውድ እየሆነ መምጣቱን ስለምታውቅ ነው። እሷም ይህ ጫና ተሰምቷታል፤ ለውጥ ለማምጣትም ዝግጁ ነች። የመንግስትን አቅም በብልሃትና በብቃት በመጠቀም የዲሲ ነዋሪዎች የሚገጥሟቸውን ችግሮች መፍታት እንደምንችል ታምናለች። ሉዊስ ጆርጅ የዲሲ ነዋሪዎችን ሕይወት ለማሻሻል ከማንኛውም አካል ጋር በጋራ የምትሰራ ሲሆን፥ በነዋሪዎቻችን ላይ ጉዳት የሚያደርስን ማንኛውንም አካል ደግሞ በፅናት ትጋፈጣለች።