ለአጠቃላይ ምርጥ ትምህርት ቤቶች

በዲሲ የሚታየው ከፍተኛ ከትምህርት የመቅረት እና የረጅም ጊዜ ከአንደኛ ደረጃ ከትምህርት ገበታ መለየት ተቀባይነት የለውም። ጃኒስ የትምህርት መቅረት ሪፈራል ስርዓቱን በማዋሃድ እና አንድ ኤጀንሲ ብቻ ኃላፊነቱን እንዲወስድ በማድረግ ሂደቱን ታቀልጣለች። ደህንነቱ የተጠበቀ እና አዳጊ የሆኑ ከትምህርት ሰዓት በኃላ  ፕሮግራሞች ለወጣቶች ምን ያህል ጠቃሚ  እንደሆኑ በራሷ ተሞክሮ ስለምታውቅ፣ እነዚህን ፕሮግራሞች በስምንቱም ወረዳዎች (wards) ታሰፋለች። ሌዊስ ጆርጅም ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ እንዲቆዩ የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ፣ ይህም የልዩ ፍላጎት ትምህርት አገልግሎቶችን፣ በትምህርት ቤት ውስጥ የሚሰጡ የአእምሮ ጤና ድጋፎችን እና በበቂ ሰራተኞች የተደራጁ ትምህርት ቤቶችን ማግኘታቸውን ታረጋግጣለች። ጥራት ያለው ትምህርት የሚጀምረው በሰው ኃይል እንደሆነ ስለምታምን፣ የሁሉንም ተማሪዎች ፍላጎት የሚያሟሉ ባለሙያዎች መኖራቸውን ለማረጋገጥ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ያለውን የሰው ኃይል ማስፋፋት አስፈላጊ መሆኑን ትረዳለች።

ሰዎችን ቅድሚያ የሚሰጥ መድረክ