ደህንነታቸው የተጠበቀ ማህበራዊ ቦታ ለሁሉም

ሉዊስ ጆርጅ የመከላከል፣ ጣልቃ የመግባት እና ህግን የማስከበር ስራዎችን ያካተተ አጠቃላይ የህዝብ ደህንነት ስትራቴጂ ተግባራዊ ታደርጋለች። ይህ በዎርድ 4 የምክር ቤት አባል በነበረችበት ወቅት በኬኔዲ ስትሪት እና በፔትዎርዝ የሚታዩ የወንጀል ድርጊቶችን ለመፍታት የተጠቀመችበት አካሄድ ነው። እንዲሁም በዲሲ የአቃቤ ህግ ቢሮ  ውስጥ አቃቤ ህግ በነበረችበት ወቅት የተከተለችው ዘዴ ነው። ከንቲባ ስትሆንም የህዝብ ደህንነትን የማረጋገጥ ስራ የአንድ ተቋም ብቻ ሳይሆን የመላው መንግስት የጋራ ሃላፊነት ይሆናል።

የሉዊስ ጆርጅ (Lewis George) የህዝብ ደህንነት መድረክ ዋና አካል የሆኑት የ”ማህበረሰብ ማዕከላት” (Community Hubs) መፍጠር ነው – እነዚህም ሰዎችን እና ሀብቶችን በአንድ ላይ የሚያገናኙ ቦታዎች ናቸው። ሁላችንም እንደምናውቀው ዲሲ  በሀብት የበለፀገች ቢሆንም በቅንጅት በኩል ግን ደካማ ናት። እሷም አሁን ያለውን መሠረተ ልማት እና ሀብት መሠረት በማድረግ ይህንን ጉድለት የምታስተካክል ሲሆን በስምንቱም ክፍለ ከተሞች ወይም ወረዳ ውስጥ የማህበረሰብ ማዕከላትን ትገነባለች። እነዚህ ማዕከላት ቤተሰቦችን እና ወጣቶችን የሚያገለግሉ፣ ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ አስደሳች እና እውቀት የሚያስጨብጡ ይሆናሉ። ማዕከላቱ እንደ የሥራ ፕሮግራሞች እና የአእምሮ ጤና አገልግሎቶች ካሉ የከተማዋ አገልግሎቶች ጋር ለመገናኘት እንደ ማዕከላዊ ቦታዎች ያገለግላሉ። ማዕከላቱ ከማህበረሰብ አቀፍ ድርጅቶች ጋር አጋርነት ስለሚፈጥሩ፣ ማህበረሰቡ እንዲበለጽግ የሚያስፈልጉትን ነገሮች እንዲያገኝ ያደርጋሉ። የበለጸጉ እና በቂ ግብዓት ያላቸው ሲሆኑ ማህበረሰቦች ደህንነታቸው በጣም የተጠበቀ ይሆናል።

ሰዎችን ቅድሚያ የሚሰጥ መድረክ