ለሁሉም የህፃናት እንክብካቤ

ዲሲ በሀገሪቱ ከፍተኛው የህጻናት እንክብካቤ ወጪ ያለበት ከተማ ነው። በተቸማርም፣ ብዙ የቀድሞ  የሕፃናት መዋዓ መምህራን የሚያገኙት  ደመወዝ በጣም ዝቅተኛ ነዉ።  ሁሉን አቀፍ ተመጣጣኝ የህጻናት እንክብካቤን መተግበር በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች የዋጋ ንረት ባለበት በዚህ ወቅት በጀታቸውን እንዲያስተካክሉ ይረዳል፣ እንዲሁም ለእያንዳንዱ የዲሲ ልጅ ጠንካራ የህይወት ጅምርን ይሰጣል። የጃኒስ እቅድ የሚከተሉትን ያከናውናል፦

ተጨማሪ ቤተሰቦችን ማዳረስ። እያንዳንዱ ቤተሰብ ለህጻናት እንክብካቤ እርዳታ ብቁ የሚሆን ሲሆን ለዚሁ አገልግሎት ከቤተሰባቸው ገቢ 7% የማይበልጥ ወጪ ያደርጋሉ፤ በዚህም ብዙ ቤተሰቦች ያነሰ ክፍያ የሚከፍሉ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ ምንም አይከፍሉም። ቤተሰቦች አሁንም ማመልከቻ ማቅረብ እና የሚፈልጉትን የህጻናት እንክብካቤ መስጫ ቦታ መምረጥ ይችላሉ።

የህፃናት ክብካቤ አቅርቦትን ማሳደግ። ጃኒስ መደበኛ ያልሆኑ ሰዓታትን የሚያገለግሉ አቅራቢዎችን ለማስፋፋት ኢንቨስትመንቶችን ታሳድጋለች፤ የቤተሰብ፣ የጓደኛ እና የጎረቤት ክብካቤን (Family, Friend, and Neighbor Care) ትመሰርታለች፤ እንዲሁም ለተቋማት ግንባታ የሚውል ልዩ የገንዘብ ድጋፍ ፈንድ ታቋቁማለች። በተጨማሪም ፕሮግራሞችን በበቂ ሁኔታ ጥቅም ላይ ባልዋሉ የትምህርት ቤት ህንፃዎች እና በዲስትሪክቱ ባለቤትነት ስር ባሉ ተቋማት ውስጥ አብረው እንዲሰሩ ታደርጋለች።

በሰው ኃይል ላይ ኢንቨስት ማድረግ። ጃኒስ ለጥሩ ደመወዝ ዋስትና የሚሆን ቀደምት የልጅነት ጊዜ መምህራን የክፍያ እኩልነት የገንዘብ ምደባን  (Early Childhood Educator Pay Equity Fund) ታጠናክራለች፤ እንዲሁም ጥሩና ደህንነታቸው የተጠበቀ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር ከሠራተኛ ማህበራት (ዩንየን) ጋር አብራ ትሠራለች። በተጨማሪም በተመጣጣኝ ዋጋ በሚሰጡ የቀደምት የልጅነት ጊዜ ትምህርት የዲግሪ እና የሰርተፍኬት ፕሮግራሞች ላይ የተማሪዎች ምዝገባ እንዲጨምር ታደርጋለች።

ዲሲ (DC) ሁሉን አቀፍ የቅድመ-መደበኛ ትምህርት (Pre-K 3 እና Pre-K 4)፣ ከልደት እስከ ሦስት ዓመት እና የደመወዝ እኩልነት የገንዘብ ምደባ  (Pay Equity Fund) ፕሮግራሞችን በስኬት በመተግበር፣ ደፋር ኢንቨስትመንቶች ውጤታማ መሆናቸውን አረጋግጧል። አሁን ደግሞ ዲሲ ሁሉን አቀፍ እና ተመጣጣኝ የሕፃናት እንክብካቤን (Universal Childcare) በመተግበር በድጋሚ ቀዳሚነቱን ሊያሳይ ይገባል።

አለም አቀፍ ተመጣጣኝ የህጻናት እንክብካቤ ማብራሪያውን ይመልከቱ

ሃምሳ አንደኛው አንቀፅ ላይ ያለውን ጽሑፍ አንብቡ

ሰዎችን ቅድሚያ የሚሰጥ መድረክ