ለአነስተኛ ንግዶች በሙሉ ቢሮክራሲን መቀነስና ኪራይን መደጎም።
ሉዊስ ጆርጅ ዲሲ ትናንሽ ንግዶችን ለመርዳት ተጨማሪ ስራዎችን መስራት እንዳለበት ትረዳለች። በአሁኑ ጊዜ ዲሲ በመንገድ ዳር የምግብ ቤቶች (streateries) ላይ ከልክ ያለፈ ደንቦችን በመጫን እና አላስፈላጊ የሆኑ የሰነድ ስራዎችን በማብዛት የንግድ ባለቤቶችን እያስቸገረች ትገኛለች። እሷም ልክ በዋርድ 4 እንዳደረገችው ሁሉ ንግዶች እንዲከፈቱና ቀጣይነት እንዲኖራቸው ትረዳለች። ይህንንም የምታደርገው አላስፈላጊ ቢሮክራሲን ለመቀነስ እና ሂደቱን ለማቀላጠፍ ለፈቃድ አሰጣጥ አገልግሎት የሚውል “አንድ ማዕከል” (one-stop shop) በማቋቋም ነው። ሉዊስ ጆርጅ የግብር ቅናሾችን በማስፋፋት እና ተጨማሪ የንግድ ቦታዎች እንዲገኙ በማድረግ፣ በቤት ኪራይ ጭማሪ ለሚቸገሩ ትናንሽ ንግዶች ተጨማሪ ድጋፍ ታደርጋለች።