የተመቻቸ ቤት ለሁሉም
እንደ ከንቲባ፣ ሉዊስ ጆርጅ ለሁሉም የገቢ ደረጃዎች የሚመጥኑ ቤቶችን ትገነባለች። መሰናክሎችን በማስወገድ፣ በተለያዩ ቦታዎች የተለያዩ የቤት አይነቶች እንዲገነቡ በመፍቀድ እና በትራንስፖርት መስመሮች አቅራቢያ ግንባታዎችን በማካሄድ የቤት አቅርቦትን ታሰፋለች። በገበያው ላይ ብቻ ከመደገፍ ይልቅ፣ በእርግጥም ተመጣጣኝ ለሆኑ ቤቶች ቅድሚያ በመስጠት የተሻሉ ቤቶችን ትገነባለች። የኪራይ ዋጋን ከመቀነስ ጀምሮ የቤት ባለቤት የመሆን እድሎችን እስከማስፋፋት ድረስ፣ መንግስት የመፍትሄው ንቁ አካል መሆን እንዳለበት ትረዳለች።
ሉዊስ ጆርጅ (Lewis George) የመንግስት ይዞታ የሆኑና የተለያየ የገቢ ደረጃ ያላቸው ዜጎች የሚኖሩባቸው ማህበራዊ ቤቶችን ትገነባለች፤ የቤት ኪራይ ገቢንም ትርፍን ለመጨመር ሳይሆን ወጪዎችን ለመቀነስ መልሳ በሥራ ላይ ታውላለች። በተጨማሪም ቤተሰቧ አሁን የሚኖሩበትን ቤት እንዲገዙ የረዳውን የኪራይ ቤቶች ግዢ አዋጅን (Tenant Opportunity to Purchase Act(ቶፓ)) በማጠናከር እና የዲሲን የመጀመሪያ ጊዜ ቤት ገዢዎች ፕሮግራም ተደራሽነትና ድጋፍ በማስፋፋት ቤተሰቦች የቤት ባለቤት እንዲሆኑ እገዛ ታደርጋለች።